tg-me.com/nibab_lehiwot/178
Last Update:
የእኔ ታሪክ (ምዕራፍ-2)
ክፍል-14
አወ እኔ ነኝ የራቢያ የድሮ ፍቅረኛ የአንተም አባት .....
ማለት አልገባኝም አባባ በሽታው ነው ወይስ በትክክል ጤነኛ ኖት ? አሌፍ ግራ ገብቶታል...የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ ....በዛ ሰዓት ውሸቱን እንደሆነ ማመን ብቻ ነበር የፈለገው ወደ ራቢያ በድጋሚ ደወለ...... ራቢያ ፈራችው የሆነ ነገር እንደተፈጠረ ልቧ ነግሯታል .......ልጄ.. አለች ፈራ ተባ እያለች
እማዬ አባቴ ማን ነው ???? ቀጥተኛ መልስ ነው ምፈልገው ምንም እንዳታስተባብይ....ቶሎ በይ.....ራቢያ በቁሟ ራደች። እ...ቆይ አንዴ..... እሱ......እማዬ ዝም በይ!!!! አሌፍ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ጮኸባት። አባቴ አቶ ሕዝቅኤል ነው አይደለ??? መልሽልኝ እንጅ አወ ወይም አይደለም በይኝ ወላሒ ለአዚም ካልሆነ ደግመሽ አይኔን አታይው!! የአሌፍ ጩኸት ሕዝቅኤልን ራሱ በትንሹ አስፈራው። ራቢያ አማራጭ ስላልነበራት "አወ" አለች። ረጋ ባለ ድምፅ አሌፍ የሚያደርገውን አጣ.....እማየ አሁንስ አንቺን መቋቋም በቃኝ!! አልቻልኩም ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘግቶ የወንድ ልጅ እንባ መታየት የለበትም የሚለውን አባባል እዛው ሻረው። ሕዝቅኤል ለማፅናናት እጁን ሰደደ። እንዳትነካኝ!!! እሱም ላይ ጮኸ እኔ አንድ አባት ብቻ ነው ያለኝ እሱም ሞቷል በቃ!! ማናችሁንም አልፈልግም አላምናችሁም ሁላችሁም ውሸታሞች ናችሁ.....አሌፍ ብሶቱን አንድ ላይ ዘረገፈው።
ቪቪያን ሲጯጯሁ በመስኮት በኩል ስታያቸው ስለነበረ በሩን ከፍታው ገባች። አሌፍ እያለቀሰ ነበር....ምንድን ነው አሌፍ አለች አንዴ አባቷን አንዴ እሱን እየተመለከተች።
ሕዝቅኤል በደከመ ድምፁ ሊያፅናናው ቢሞክርም አሌፍ ጭራሽ መረጋጋት እየተሳነው መጣ ። ቪቪያን ወደሱ ስትጠጋ እንዳትነኪኝ እህቴ እያለ ሳቅ እና ለቅሶ ባዘለ ድምፅ ጮኸ!!!
ምንድን ነው አባዬ ራቢያ አፈጠጠችበት። በቃችሁ ዝም በሉ!!! ሕዝቅኤልም የቁጣ ጩኸቱን ለቀቀው ።(ሜሮን እና ኤልሳ ከውጭ ዶክተሮች እንዳይመጡ እየተጠባበቁ ነው። ማቲያስ ደግሞ ያልታወቀ ስልክ ተደውሎለት ሊያናግር እንደወጣ አልተመለሰም)
በሕዝቅኤል ቁጣ ክፍሉ ፀጥ አለ ያሁሉ ጩኸት በአንድ ጊዜ ጠፋ። ተቀመጡ ሁለታችሁም .....ቪቪያን እና አሌፍ የታዘዙትን አደረጉ። አንቺ ዝም በይ ምንም ድምፅ አልፈልግም። አንተ ደሞ ሙሉ ታሪክህን ስማና የምታደርገውን ታደርጋለህ....ትልቅ ሰው ነህ ከምንም ነገር ከልክየ አላድንህም። ከቁጣው የተነሳ ብቻ ሳይሆን ሊናገር ያሰበውን ነገር ቀድሞ የታወቃት ይመስል የቪቪያን እጆች መንቀጥቀጥ ጀምረዋል።
ሕዝቅኤል ለቪቪያን የነገራትን ሙሉ ታሪክ ለ አሌፍ አንድ በአንድ ነገረው። አወ በንግግሩ ቪቪያን አሌፍ ወንድሟ እንደሆነ አወቀች። ልቧ ስብርብር አለ፣ ክንፏን እንደተመታች ወፍ እዛው ባለችበት ተልፈሰፈሰች። እንደዛ ልታገኘው ስትጓጓለት የነበረችው ወንድሟ፣ እንደዛ አቅፎ እንደ ታናሽ እህቱ ፀጉሯን እንዲነካካት የምትመኘው ሰው የምታፈቅረው አሌፍ ነው። ገና ዛሬ ወንድሜ ባይሆንስ ለዘለዓለም ሳላገኘው ብቀር ብላ ተመኘች።
አሌፍ ሙሉ ታሪኩን ከሰማ በኋላ ምን አደረግን? ቆይ በምን ጥፋታችን ነው እንደዚህ የምታሰቃዩን? ምን አይነት ህይወት ነው የሰጣችሁን?? እህቴን እንዳፈቅር ኧረ ጭራሽ ባላውቅማ አግብቻት እንድኖር? ለምን???አሌፍ ከልቡ አምርሮ ሕዝቅኤልን መናገር ጀመረ።
ሕዝቅኤል እስኪጨርስ ዝም አለው። ቪቪያን ተናገሪ እንጅ ለምን ዝም ትያለሽ እያለ በእጁ ይገፋፋታል።ፈርተሽ ነው? የአሌፍ እንባ እንደ ጎርፍ ይወርዳል። ቪቪያን ግን ደንዝዛለች አትናገርም፣ አታለቅስም፣ ፀጥ ፍዝዝ፣ ብቻ።
ለ እኛስ ቀላል ነው? ብለህ ታስባለህ ኧ እስኪ ራቢያን ተመልከታት። ለ አንተ ብላ አይደለም በጊዜው የማትወደውን ሰው ያገባችው? ኧ አንተን ማስወጣት እና በሰላም ከቤተሰቧ ጋር መኖር አቅቷት ይመስልሃል? መልስልኝ?? አየህ ከክብሯ ፣ ከቤተሰቧ፣ ከማህበረሰቡ አንተን ስላስበለጠች እንጅ እንደ አንድ ተራ ሰው በ 2 እና 3 ሺ ብር አሽቀንጥራ ጥላህ እስካሁን ህልሟን አሳክታ እየኖረች ነበር። ይሄን እንዴት ማሰብ ያቅትሃል ስቃይዋ አይታይህም? ላንተ ስትል የተሸከመችው መከራ አይታይህም ወይ? ልታዝንላት ነበርኮ የሚገባው ....ምን ልትል እንዳሰብክ ይገባኛል" እኔ ፈልጌ አልመጣሁም" ልትል ነው አይደለ እንግዲያውስ እኔም ልንገርህ እኛም ፈልገን አልነበረም ያመጣንህ ድንገት ሳናስበው በተሰራ የአንድ ቀን ስህተት ነበር። ራቢያኮ አንተን ለመግደል ብዙ ምክኒያቶች ነበሯት። ጭራሽ እንደተፈጠርክ ለ እኔ ሳትነግረኝ ብቻዋን ስቃዩን ተሸከመችው። ለ አንተ ብቻ ሳይሆን እንደነገርኩህ ለ እኔም ታስብ ነበር። እስኪ አንድ ቀን በአንተ መወለድ ስታማርር ሰምተሃት ታውቃለህ? ወደኋላ ጎተትከኝ ብላህ ታውቃለች?? ሳትፈለግ የመጣህ ስህተት ....ብላህ ታውቃለች ወይ ንገረኝ?
አሌፍ አንገቱን ደፍቶ ፀጥ አለ።(ራቢያ ለ 50ኛ ጊዜ እየደወለች ነው።)
ታዲያ እኔስ አላሳዝንም ይሄ ሁሉ ሚስጥር ተደብቆብኝ ኖርኩ። ጭራሽ እህቴን አፈቀርኳት ከዛ ድንገት መጥታችሁ እህትህ ነች አላችሁኝ። ከዛስ....ቆይ አግብቻትስ ቢሆን...
ለሱ ነውኮ ፈጣሪን አመስግን የምልህ ቢያንስ የእኛን ታሪክ አልደገማችሁም። ለበጎ ነው ያገናኛችሁ ብለህ ተቀበል። አሌፍ ልጄ ከልጅነትህ ጀምሮ ባውቅህ እና ብንከባከብህ ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር።ግን አልተፈቀደልንም ምን ማድረግ እንችል ነበር ሁላችንም የራሳችን ሕመም አለብን።
ይሔንን ሁሉ ለአሌፍ ሲያወራ ቪቪያንን ረስቷት ነበር። ወደሷ ዞሮ እርግብ ነይ ወደዚህ አላት ደመነፍሷን ሔዳ ታቀፈችው።
አሌፍም ተነስቶ ሔዶ ታቀፈው። ሕዝቅኤል በጣም ደነገጠ፣ ደስታም ተጨመረበት። እንደዚህ ይፈጠራል ብሎ በጭራስ አስቦት አያውቅም ነበር። ሁለቱን ልጆቹን በቀኝ እና በግራው አቅፎ የደስታ እንባን አነባ። ከብዙ አመታት በኋላ የተጣላውን ፈጣሪውን ቀና ብሎ በእንባ አይኑ አመሰገነው። ልጆቼ እርስ በርስ ተጠባበቁ። አለ በየተራ ግንባራቸውን እየሳመ።ከዚያም አይኖቹንም ሸፈነ። ያቀፏቸው እጆች ከትከሻቸው ሲንሸራተቱ ቪቪያን እና አሌፍ ቀና አሉ።
ይቀጥል ይሆናል........
@nibab_lehiwot
BY ሕይወትን - በገፅ
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/nibab_lehiwot/178